Psalms 95

የየዕለቱ መዝሙር

1ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤
በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።
2ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤
በዝማሬም እናወድሰው።

3 እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤
ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።
4የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤
የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።
5እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።

6ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤
በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤
7እርሱ አምላካችን ነውና፤
እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣
የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።

ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
8በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣
ማሳህ ፈተና ማለት ነው።

በመሪባም
መሪባ ጠብ ማለት ነው።
እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።
9ሥራዬን ቢያዩም፣
አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።
10ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤
እኔም፣ “ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤
መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።
11ስለዚህ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብዬ፣
በቍጣዬ ማልሁ።
Copyright information for AmhNASV